-
2 ነገሥት 23:8, 9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ከዚያም ካህናቱን ሁሉ ከይሁዳ ከተሞች አስወጣ፤ እንዲሁም ካህናቱ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን ከጌባ+ አንስቶ እስከ ቤርሳቤህ+ ድረስ የሚገኙትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች አረከሰ። በተጨማሪም የከተማዋ አለቃ በሆነው በኢያሱ መግቢያ በር ላይ ይኸውም አንድ ሰው በከተማዋ በር ሲገባ በስተ ግራ በኩል በሚያገኘው በር ላይ የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች አፈራረሰ። 9 ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች ካህናት፣ በኢየሩሳሌም በሚገኘው የይሖዋ መሠዊያ አያገልግሉ+ እንጂ ከወንድሞቻቸው ጋር ቂጣ* ይበሉ ነበር።
-
-
ነህምያ 9:34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
34 ነገሥታታችን፣ መኳንንታችን፣ ካህናታችንም ሆኑ አባቶቻችን ሕግህን አልጠበቁም፤ ደግሞም እነሱን ለማስጠንቀቅ ብለህ ለሰጠሃቸው ትእዛዛትም ሆነ ማሳሰቢያዎች ትኩረት አልሰጡም።*
-