መዝሙር 51:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አምላክ ሆይ፣ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤+በውስጤም ጽኑ የሆነ አዲስ መንፈስ አኑር።+ ኤርምያስ 32:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 ለእነሱም ሆነ ከእነሱ በኋላ ለሚመጡት ልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ዘወትር እኔን እንዲፈሩ+ አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።+ ሕዝቅኤል 11:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እኔም አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤+ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አኖራለሁ፤+ ድንጋይ የሆነውንም ልብ ከሰውነታቸው አውጥቼ+ የሥጋ ልብ* እሰጣቸዋለሁ፤+ ኤፌሶን 4:23, 24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ደግሞም አእምሯችሁን የሚያሠራው ኃይል* እየታደሰ ይሂድ፤+ 24 እንዲሁም እንደ አምላክ ፈቃድ የተፈጠረውንና ከእውነተኛ ጽድቅና ታማኝነት ጋር የሚስማማውን አዲሱን ስብዕና* መልበስ ይኖርባችኋል።+
23 ደግሞም አእምሯችሁን የሚያሠራው ኃይል* እየታደሰ ይሂድ፤+ 24 እንዲሁም እንደ አምላክ ፈቃድ የተፈጠረውንና ከእውነተኛ ጽድቅና ታማኝነት ጋር የሚስማማውን አዲሱን ስብዕና* መልበስ ይኖርባችኋል።+