ዘፀአት 19:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የሲና ተራራ ይሖዋ በእሳት ስለወረደበት ዙሪያውን ጨሰ፤+ ጭሱም እንደ እቶን ጭስ እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ በኃይል ተናወጠ።+ መዝሙር 97:2, 3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ደመናና ድቅድቅ ጨለማ በዙሪያው አለ፤+ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።+ 3 እሳት በፊቱ ይሄዳል፤+ጠላቶቹንም በሁሉም አቅጣጫ ይፈጃል።+