ኢሳይያስ 58:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 58 “ጉሮሮህ እስኪሰነጠቅ ጩኽ፤ ምንም አትቆጥብ! ድምፅህን እንደ ቀንደ መለከት አሰማ። ለሕዝቤ ዓመፃቸውን፣ለያዕቆብ ቤት ኃጢአታቸውን አውጅ።+ ሕዝቅኤል 33:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተን ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው።+