ኢሳይያስ 21:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከዚያም እንደ አንበሳ ጮኾ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በየቀኑ በመጠበቂያው ግንብ ላይ ቆሜአለሁ፤በየሌሊቱም በጥበቃ ቦታዬ ላይ ተሰይሜአለሁ።+ ኤርምያስ 1:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 አንተ ግን ለሥራ ተዘጋጅ፤*ደግሞም ተነስ፤ እኔ የማዝህንም ሁሉ ንገራቸው። እኔ ራሴ በፊታቸው እንዳላሸብርህ፣እነሱን አትፍራቸው።+ ሕዝቅኤል 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤+ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው።+