ኢሳይያስ 26:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ሕዝቤ ሆይ፣ ሂድ ወደ ውስጠኛው ክፍልህ ግባ፤በርህንም ከኋላህ ዝጋ።+ ቁጣው* እስኪያልፍ ድረስለጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።+ ኢዩኤል 2:31, 32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን+ ከመምጣቱ በፊትፀሐይ ወደ ጨለማ፣ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።+ 32 የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤+ይሖዋ እንደተናገረው በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚድኑ+ ይኸውምይሖዋ የሚጠራቸው ከጥፋት የሚተርፉ ሰዎች ይኖራሉ።” ማቴዎስ 24:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሆኖ የማያውቅ ዳግመኛም የማይሆን+ ታላቅ መከራ+ ይከሰታል። 22 እንዲያውም ቀኖቹ ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ ሁሉ ባልዳነ ነበር፤ ሆኖም ለተመረጡት ሲባል ቀኖቹ ያጥራሉ።+ ራእይ 7:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከሽማግሌዎቹ አንዱ መልሶ “እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱት+ እነማን ናቸው? ከወዴትስ የመጡ ናቸው?” አለኝ። 14 እኔም ወዲያውኑ “ጌታዬ፣ የምታውቀው አንተ ነህ” አልኩት። እሱም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ታላቁን መከራ+ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል።+
31 ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን+ ከመምጣቱ በፊትፀሐይ ወደ ጨለማ፣ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።+ 32 የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤+ይሖዋ እንደተናገረው በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚድኑ+ ይኸውምይሖዋ የሚጠራቸው ከጥፋት የሚተርፉ ሰዎች ይኖራሉ።”
21 ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሆኖ የማያውቅ ዳግመኛም የማይሆን+ ታላቅ መከራ+ ይከሰታል። 22 እንዲያውም ቀኖቹ ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ ሁሉ ባልዳነ ነበር፤ ሆኖም ለተመረጡት ሲባል ቀኖቹ ያጥራሉ።+
13 ከሽማግሌዎቹ አንዱ መልሶ “እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱት+ እነማን ናቸው? ከወዴትስ የመጡ ናቸው?” አለኝ። 14 እኔም ወዲያውኑ “ጌታዬ፣ የምታውቀው አንተ ነህ” አልኩት። እሱም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ታላቁን መከራ+ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል።+