መሳፍንት 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ስለዚህ እስራኤላውያን በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤ አምላካቸውን ይሖዋንም ረሱ፤ ባአልንና+ የማምለኪያ ግንዶችን* + አገለገሉ። 1 ነገሥት 16:30-32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 የኦምሪ ልጅ አክዓብ ከእሱ በፊት የነበሩት ሁሉ ከፈጸሙት የከፋ ድርጊት በይሖዋ ፊት ፈጸመ።+ 31 አክዓብ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና መመላለሱ ሳያንሰው የሲዶናውያን+ ንጉሥ የኤትባዓል ልጅ የሆነችውን ኤልዛቤልን+ አገባ፤ እንዲሁም ባአልን ማገልገልና+ ለእሱ መስገድ ጀመረ። 32 እንዲሁም በሰማርያ ለባአል በሠራው ቤት+ ውስጥ* ለባአል መሠዊያ አቆመ። 2 ነገሥት 10:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በዚህ መንገድ ኢዩ ባአልን ከእስራኤል አስወገደ። ሆሴዕ 11:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እነሱ* ደጋግመው በጠሯቸው መጠንበዚያው ልክ ከእነሱ ራቁ።+ ለባአል ምስሎች መሠዋታቸውን፣+ለተቀረጹት ምስሎችም መሥዋዕት ማቅረባቸውን ቀጠሉ።+
30 የኦምሪ ልጅ አክዓብ ከእሱ በፊት የነበሩት ሁሉ ከፈጸሙት የከፋ ድርጊት በይሖዋ ፊት ፈጸመ።+ 31 አክዓብ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና መመላለሱ ሳያንሰው የሲዶናውያን+ ንጉሥ የኤትባዓል ልጅ የሆነችውን ኤልዛቤልን+ አገባ፤ እንዲሁም ባአልን ማገልገልና+ ለእሱ መስገድ ጀመረ። 32 እንዲሁም በሰማርያ ለባአል በሠራው ቤት+ ውስጥ* ለባአል መሠዊያ አቆመ።