የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መሳፍንት 2:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ይሖዋን ትተው ባአልንና የአስታሮትን ምስሎች አገለገሉ።+

  • መሳፍንት 3:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ስለዚህ እስራኤላውያን በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤ አምላካቸውን ይሖዋንም ረሱ፤ ባአልንና+ የማምለኪያ ግንዶችን* + አገለገሉ።

  • 1 ነገሥት 16:30-32
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 የኦምሪ ልጅ አክዓብ ከእሱ በፊት የነበሩት ሁሉ ከፈጸሙት የከፋ ድርጊት በይሖዋ ፊት ፈጸመ።+ 31 አክዓብ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና መመላለሱ ሳያንሰው የሲዶናውያን+ ንጉሥ የኤትባዓል ልጅ የሆነችውን ኤልዛቤልን+ አገባ፤ እንዲሁም ባአልን ማገልገልና+ ለእሱ መስገድ ጀመረ። 32 እንዲሁም በሰማርያ ለባአል በሠራው ቤት+ ውስጥ* ለባአል መሠዊያ አቆመ።

  • 1 ነገሥት 18:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 ይልቅስ አሁን እስራኤላውያንን በሙሉ፣ ከኤልዛቤል ማዕድ ከሚበሉት 450 የባአል ነቢያትና 400 የማምለኪያ ግንድ*+ ነቢያት ጋር በቀርሜሎስ+ ተራራ ላይ ሰብስብልኝ።”

  • 2 ነገሥት 17:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ይሖዋ በነቢያቱ ሁሉና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ+ አማካኝነት እስራኤልንና ይሁዳን “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ!+ አባቶቻችሁን ባዘዝኳቸውና በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ለእናንተ በሰጠሁት ሕግ መሠረት ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ጠብቁ” በማለት በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር።

  • 2 ነገሥት 17:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 የአምላካቸውን የይሖዋን ትእዛዛት በሙሉ ተዉ፤ ለራሳቸውም ከብረት የተሠሩ ሁለት የጥጃ ሐውልቶችን* አበጁ፤+ የማምለኪያም ግንድ*+ ሠሩ፤ ለሰማያት ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፤+ እንዲሁም ባአልን አገለገሉ።+

  • ሆሴዕ 2:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ለባአል ምስሎች መሥዋዕት ባቀረበችባቸው፣+ በጉትቻዋና በጌጦቿ በተንቆጠቆጠችባቸው

      እንዲሁም አጥብቀው የሚወዷትን በተከተለችባቸው ቀናት የተነሳ ተጠያቂ አደርጋታለሁ፤

      እኔንም ረስታኝ ነበር’+ ይላል ይሖዋ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ