15 ሥርዓቶቹን፣ ከአባቶቻቸው ጋር የገባውን ቃል ኪዳንና+ እነሱን ለማስጠንቀቅ የሰጣቸውን ማሳሰቢያዎች ችላ አሉ፤+ ደግሞም ይሖዋ የእነሱን ምሳሌ እንዳይከተሉ ያዘዛቸውን+ በዙሪያቸው ያሉትን ብሔራት በመምሰል ከንቱ ጣዖቶችን ተከተሉ፤+ እነሱ ራሳቸውም ከንቱ ሆኑ።+
16 የአምላካቸውን የይሖዋን ትእዛዛት በሙሉ ተዉ፤ ለራሳቸውም ከብረት የተሠሩ ሁለት የጥጃ ሐውልቶችን አበጁ፤+ የማምለኪያም ግንድ+ ሠሩ፤ ለሰማያት ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፤+ እንዲሁም ባአልን አገለገሉ።+