19 እነሱ ኔጌብንና የኤሳውን ተራራማ ምድር፣+
ሸፌላንና የፍልስጤምን ምድር ይወርሳሉ።+
የኤፍሬምን መሬትና የሰማርያን መሬት ይወርሳሉ፤+
ቢንያምም ጊልያድን ይወርሳል።
20 እስከ ሰራፕታ+ ድረስ ያለው የከነአናውያን ምድር፣
ከዚህ የመከላከያ ግንብ በግዞት የተወሰዱት ሰዎች+ ይኸውም የእስራኤል ሕዝብ ይዞታ ይሆናል።
በሰፋራድ የነበሩት ከኢየሩሳሌም በግዞት የተወሰዱ ሰዎችም የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።+