መዝሙር 34:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ክፉ ከሆነ ነገር ራቅ፤ መልካም የሆነውንም አድርግ፤+ሰላምን ፈልግ፤ ተከተለውም።+ መዝሙር 97:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እናንተ ይሖዋን የምትወዱ፣ ክፉ የሆነውን ነገር ጥሉ።+ እሱ የታማኝ አገልጋዮቹን ሕይወት* ይጠብቃል፤+ከክፉዎች እጅ* ይታደጋቸዋል።+ ሮም 12:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ፍቅራችሁ ግብዝነት የሌለበት ይሁን።+ ክፉ የሆነውን ተጸየፉ፤+ ጥሩ የሆነውን አጥብቃችሁ ያዙ።