መዝሙር 97:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እናንተ ይሖዋን የምትወዱ፣ ክፉ የሆነውን ነገር ጥሉ።+ እሱ የታማኝ አገልጋዮቹን ሕይወት* ይጠብቃል፤+ከክፉዎች እጅ* ይታደጋቸዋል።+ ምሳሌ 8:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሖዋን መፍራት ማለት ክፉ ነገርን መጥላት ነው።+ ትዕቢትን፣ ኩራትን፣+ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ።+