መዝሙር 147:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ይገነባል፤+የተበተኑትን የእስራኤል ነዋሪዎች ይሰበስባል።+ ኢሳይያስ 56:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 የተበተኑትን የእስራኤል ሰዎች የሚሰበስበው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ+ እንዲህ ይላል፦ “አስቀድሞ ከተሰበሰቡት በተጨማሪ ሌሎችን ወደ እሱ እሰበስባለሁ።”+ ሕዝቅኤል 34:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የተበታተኑትን በጎቹን አግኝቶ እንደሚመግብ እረኛ በጎቼን እንከባከባለሁ።+ በደመናትና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።+ ሕዝቅኤል 34:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “የጠፋውን እፈልጋለሁ፤+ የባዘነውን መልሼ አመጣለሁ፤ የተጎዳውን በጨርቅ አስራለሁ፤ የደከመውን አበረታለሁ፤ የወፈረውንና ጠንካራ የሆነውን ግን አጠፋለሁ። እፈርድበታለሁ፤ ተገቢውንም ቅጣት እሰጠዋለሁ።” ሕዝቅኤል 37:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 “ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያንን ከሄዱባቸው ብሔራት መካከል አመጣቸዋለሁ፤ ከየአቅጣጫውም ሰብስቤ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።+ ሶፎንያስ 3:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እነሆ፣ በዚያን ጊዜ በሚጨቁኑሽ ሁሉ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ፤+የምታነክሰውንም አድናታለሁ፤+የተበተነችውንም እሰበስባለሁ።+ ኀፍረት በተከናነቡበት ምድር ሁሉእንዲወደሱና ዝና* እንዲያተርፉ አደርጋቸዋለሁ።
16 “የጠፋውን እፈልጋለሁ፤+ የባዘነውን መልሼ አመጣለሁ፤ የተጎዳውን በጨርቅ አስራለሁ፤ የደከመውን አበረታለሁ፤ የወፈረውንና ጠንካራ የሆነውን ግን አጠፋለሁ። እፈርድበታለሁ፤ ተገቢውንም ቅጣት እሰጠዋለሁ።”
21 “ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያንን ከሄዱባቸው ብሔራት መካከል አመጣቸዋለሁ፤ ከየአቅጣጫውም ሰብስቤ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።+
19 እነሆ፣ በዚያን ጊዜ በሚጨቁኑሽ ሁሉ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ፤+የምታነክሰውንም አድናታለሁ፤+የተበተነችውንም እሰበስባለሁ።+ ኀፍረት በተከናነቡበት ምድር ሁሉእንዲወደሱና ዝና* እንዲያተርፉ አደርጋቸዋለሁ።