የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 86:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  9 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ የሠራሃቸው ብሔራት ሁሉ ይመጣሉ፤

      በፊትህም ይሰግዳሉ፤+

      ለስምህም ክብር ይሰጣሉ።+

  • ኢሳይያስ 2:2-4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  2 በዘመኑ መጨረሻ*

      የይሖዋ ቤት ተራራ

      ከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤+

      ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤

      ብሔራትም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።+

       3 ብዙ ሕዝቦችም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦

      “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ፣

      ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+

      እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤

      በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”+

      ሕግ* ከጽዮን፣

      የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።+

       4 እሱ በብሔራት መካከል ይፈርዳል፤

      ከብዙ ሕዝቦች ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል።*

      እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣

      ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+

      አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤

      ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+

  • ኢሳይያስ 60:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 ብሔራት ወደ ብርሃንሽ፣+

      ነገሥታትም+ አንጸባራቂ ወደሆነው ውበትሽ* ይመጣሉ።+

  • ራእይ 15:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ይሖዋ* ሆይ፣ ለመሆኑ አንተን የማይፈራና ስምህን ከፍ ከፍ የማያደርግ ማን ነው? አንተ ብቻ ታማኝ ነህና!+ የጽድቅ ድንጋጌዎችህ ስለተገለጡ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ