የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 11:11, 12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 በዚያን ቀን ይሖዋ ዳግመኛ እጁን ዘርግቶ የተረፉትን የሕዝቡን ቀሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ ከአሦር፣+ ከግብፅ፣+ ከጳትሮስ፣+ ከኢትዮጵያ፣*+ ከኤላም፣+ ከሰናኦር፣* ከሃማትና ከባሕር ደሴቶች+ መልሶ ይሰበስባል። 12 ለብሔራት ምልክት* ያቆማል፤ በየቦታው የተሰራጩትን እስራኤላውያንም መልሶ ያመጣቸዋል፤+ እንዲሁም የተበታተኑትን የይሁዳ ሰዎች ከአራቱም የምድር ማዕዘኖች ይሰበስባል።+

  • ኢሳይያስ 27:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 በዚያም ቀን የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ሰው ዛፍ ላይ ያሉ ፍሬዎችን አርግፎ አንድ በአንድ እንደሚለቅም ሁሉ፣ ይሖዋም ከታላቁ ወንዝ* አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ*+ ድረስ ባለው ቦታ ሁሉ የተበተናችሁትን ይሰበስባችኋል።+

  • ሕዝቅኤል 28:25
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 25 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ቤት ሰዎች ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል ዳግመኛ በምሰበስባቸው ጊዜ+ በብሔራት ፊት በእነሱ መካከል እቀደሳለሁ።+ እነሱም ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት+ ምድራቸው ላይ ይኖራሉ።+

  • ሕዝቅኤል 34:15, 16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 “‘“በጎቼን እኔ ራሴ አሰማራለሁ፤+ እኔ ራሴም አሳርፋቸዋለሁ”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 16 “የጠፋውን እፈልጋለሁ፤+ የባዘነውን መልሼ አመጣለሁ፤ የተጎዳውን በጨርቅ አስራለሁ፤ የደከመውን አበረታለሁ፤ የወፈረውንና ጠንካራ የሆነውን ግን አጠፋለሁ። እፈርድበታለሁ፤ ተገቢውንም ቅጣት እሰጠዋለሁ።”

  • አሞጽ 9:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+

      እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+

      የወይን ተክል ተክለው የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤+

      አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ