ኢሳይያስ 13:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከመንግሥታትም ሁሉ እጅግ የከበረችው፣*+የከለዳውያን ውበትና ኩራት የሆነችው ባቢሎን፣+አምላክ እንደገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች።+ ኤርምያስ 27:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 አሁንም እነዚህን ሁሉ አገሮች ለአገልጋዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤+ የዱር አራዊትም እንኳ እንዲገዙለት አድርጌአለሁ። 7 የእሱ መንግሥት የሚያበቃበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ+ ብሔራት ሁሉ እሱን፣ ልጁንና የልጅ ልጁን ያገለግላሉ፤ በዚያን ጊዜ ግን ብዙ ብሔራትና ታላላቅ ነገሥታት ባሪያቸው ያደርጉታል።’+ ዘካርያስ 2:7-9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “ጽዮን ሆይ፣ ነይ! ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፣ አምልጪ።+ 8 ክብር ከተጎናጸፈ በኋላ፣* እናንተን ወደዘረፏችሁ ብሔራት የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦+ ‘እናንተን የሚነካ ሁሉ የዓይኔን ብሌን* ይነካል።+ 9 አሁን በእነሱ ላይ እጄን በዛቻ አወዛውዛለሁ፤ የገዛ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል።’+ እናንተም እኔን የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ።
6 አሁንም እነዚህን ሁሉ አገሮች ለአገልጋዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤+ የዱር አራዊትም እንኳ እንዲገዙለት አድርጌአለሁ። 7 የእሱ መንግሥት የሚያበቃበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ+ ብሔራት ሁሉ እሱን፣ ልጁንና የልጅ ልጁን ያገለግላሉ፤ በዚያን ጊዜ ግን ብዙ ብሔራትና ታላላቅ ነገሥታት ባሪያቸው ያደርጉታል።’+
7 “ጽዮን ሆይ፣ ነይ! ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፣ አምልጪ።+ 8 ክብር ከተጎናጸፈ በኋላ፣* እናንተን ወደዘረፏችሁ ብሔራት የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦+ ‘እናንተን የሚነካ ሁሉ የዓይኔን ብሌን* ይነካል።+ 9 አሁን በእነሱ ላይ እጄን በዛቻ አወዛውዛለሁ፤ የገዛ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል።’+ እናንተም እኔን የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ።