የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 85:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  8 እውነተኛው አምላክ ይሖዋ የሚናገረውን እሰማለሁ፤

      እሱ ለሕዝቡና ለታማኝ አገልጋዮቹ ስለ ሰላም ይናገራልና፤+

      ብቻ እንደቀድሞው በራሳቸው ከልክ በላይ አይተማመኑ።+

  • ኢሳይያስ 2:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 እሱ በብሔራት መካከል ይፈርዳል፤

      ከብዙ ሕዝቦች ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል።*

      እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣

      ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+

      አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤

      ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+

  • ኢሳይያስ 60:17, 18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 በመዳብ ፋንታ ወርቅ፣

      በብረት ፋንታ ብር፣

      በእንጨት ፋንታ መዳብ፣

      በድንጋዮችም ፋንታ ብረት አመጣለሁ፤

      ሰላምንም የበላይ ተመልካቾችሽ፣

      ጽድቅንም አሠሪዎችሽ አድርጌ እሾማለሁ።+

      18 ከዚህ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ዓመፅ፣

      ወይም በክልልሽ ውስጥ ጥፋትና ውድመት አይሰማም።+

      ቅጥሮችሽን መዳን፣+ በሮችሽንም ውዳሴ ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ።

  • ዘካርያስ 8:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ‘የሰላም ዘር ይዘራልና፤ የወይን ተክሉ ፍሬ ያፈራል፤ ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች፤+ ሰማያትም ጠል ያዘንባሉ፤ እኔም የዚህ ሕዝብ ቀሪዎች እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንዲወርሱ አደርጋለሁ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ