የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 36:20, 21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ከሰይፍ የተረፉትንም ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤+ እነሱም የፋርስ መንግሥት* መግዛት እስከጀመረበት ጊዜ ድረስ+ የእሱና የወንዶች ልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ፤+ 21 ይህም የሆነው ይሖዋ በኤርምያስ በኩል የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣+ ምድሪቱ የሰንበት ዕዳዋን እስክትከፍል ድረስ ነው።+ ፈራርሳ በቆየችባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ 70 ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ሰንበትን አከበረች።+

  • ኤርምያስ 25:11, 12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 መላ ምድሪቱ ትወድማለች፤ እንዲሁም አስፈሪ ቦታ ትሆናለች፤ እነዚህም ብሔራት የባቢሎንን ንጉሥ 70 ዓመት ያገለግሉታል።”’+

      12 “‘ይሁንና ሰባው ዓመት ሲፈጸም+ በበደላቸው የተነሳ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ብሔር ተጠያቂ አደርጋለሁ’*+ ይላል ይሖዋ፤ ‘የከለዳውያንንም ምድር እስከ ወዲያኛው ባድማ አደርገዋለሁ።+

  • ዳንኤል 9:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 አዎ፣ በዘመነ መንግሥቱ የመጀመሪያ ዓመት እኔ ዳንኤል ለነቢዩ ኤርምያስ በተነገረው የይሖዋ ቃል ላይ በተጠቀሰው መሠረት ኢየሩሳሌም ፈራርሳ የምትቆየው+ ለ70 ዓመት+ እንደሆነ ከመጻሕፍቱ* አስተዋልኩ።

  • ዘካርያስ 7:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 “ለምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉና ለካህናቱ እንዲህ በላቸው፦ ‘ለ70 ዓመታት+ በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ዋይ ዋይ ስትሉ፣+ ትጾሙ የነበረው በእርግጥ ለእኔ ነበር?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ