የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 22:27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ይሖዋን አስታውሰው ወደ እሱ ይዞራሉ።

      የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ በፊትህ ይሰግዳሉ።+

  • ኢሳይያስ 2:2, 3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  2 በዘመኑ መጨረሻ*

      የይሖዋ ቤት ተራራ

      ከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤+

      ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤

      ብሔራትም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።+

       3 ብዙ ሕዝቦችም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦

      “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ፣

      ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+

      እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤

      በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”+

      ሕግ* ከጽዮን፣

      የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።+

  • ኢሳይያስ 11:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 በዚያን ቀን የእሴይ ሥር+ ለሕዝቦች ምልክት* ሆኖ ይቆማል።+

      ብሔራት ከእሱ መመሪያ ይሻሉ፤*+

      ማረፊያ ስፍራውም እጅግ የከበረ ይሆናል።

  • ኢሳይያስ 55:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  5 እነሆ፣ የማታውቀውን ብሔር ትጠራለህ፤

      የማያውቅህ ብሔርም ለአምላክህ ለይሖዋና ለእስራኤል ቅዱስ ሲል

      ወደ አንተ ሮጦ ይመጣል፤+

      ምክንያቱም እሱ ክብር ያጎናጽፍሃል።+

  • ኢሳይያስ 60:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 ብሔራት ወደ ብርሃንሽ፣+

      ነገሥታትም+ አንጸባራቂ ወደሆነው ውበትሽ* ይመጣሉ።+

  • ሆሴዕ 1:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 “የእስራኤልም ሕዝብ* ብዛት ሊሰፈር ወይም ሊቆጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል።+ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’+ ተብሎ በተነገራቸው ስፍራም ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ይባላሉ።+

  • ሚክያስ 4:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  2 ብዙ ብሔራትም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦

      “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራና

      ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+

      እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤

      በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”

      ሕግ* ከጽዮን፣

      የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።

  • ሐጌ 2:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 “‘ብሔራትንም ሁሉ አናውጣለሁ፤ በብሔራትም ሁሉ መካከል ያሉ የከበሩ* ነገሮች ይመጣሉ፤+ ደግሞም ይህን ቤት በክብር እሞላዋለሁ’+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ