ማቴዎስ 26:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’+ ተብሎ ስለተጻፈ በዚህች ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ላይ በሚደርሰው ነገር የተነሳ ትሰናከላላችሁ። ማቴዎስ 26:55, 56 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 55 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ የመጣችሁት እኔን ለመያዝ ነው? በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ተቀምጬ አስተምር ነበር፤+ ሆኖም ያን ጊዜ አልያዛችሁኝም።+ 56 ይህ ሁሉ የሆነው ግን በነቢያት መጻሕፍት* የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።”+ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ጥለውት ሸሹ።+ ማርቆስ 14:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “‘እረኛውን እመታለሁ፤+ በጎቹም ይበተናሉ’+ ተብሎ ስለተጻፈ ሁላችሁም ትሰናከላላችሁ። ማርቆስ 14:50 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 50 በዚህ ጊዜ ሁሉም ጥለውት ሸሹ።+ ዮሐንስ 16:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እነሆ፣ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ የምትበታተኑበትና እኔን ብቻዬን ትታችሁ የምትሄዱበት ሰዓት ቀርቧል፤+ እንዲያውም ደርሷል። ይሁንና አብ ከእኔ ጋር ስላለ ብቻዬን አይደለሁም።+
31 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’+ ተብሎ ስለተጻፈ በዚህች ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ላይ በሚደርሰው ነገር የተነሳ ትሰናከላላችሁ።
55 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ የመጣችሁት እኔን ለመያዝ ነው? በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ተቀምጬ አስተምር ነበር፤+ ሆኖም ያን ጊዜ አልያዛችሁኝም።+ 56 ይህ ሁሉ የሆነው ግን በነቢያት መጻሕፍት* የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።”+ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ጥለውት ሸሹ።+
32 እነሆ፣ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ የምትበታተኑበትና እኔን ብቻዬን ትታችሁ የምትሄዱበት ሰዓት ቀርቧል፤+ እንዲያውም ደርሷል። ይሁንና አብ ከእኔ ጋር ስላለ ብቻዬን አይደለሁም።+