ዘዳግም 24:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 “አንድ ሰው አንዲት ሴት ቢያገባ ሆኖም ነውር የሆነ ነገር አግኝቶባት ቅር ቢሰኝ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት+ ከቤቱ ያሰናብታት።+ ማቴዎስ 19:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ፈሪሳውያንም ወደ እሱ መጥተው ሊፈትኑት በማሰብ “አንድ ሰው በማንኛውም ምክንያት ሚስቱን እንዲፈታ ሕግ ይፈቅድለታል?” ሲሉ ጠየቁት።+ ማቴዎስ 19:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሴ የልባችሁን ደንዳናነት አይቶ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ፈቀደላችሁ+ እንጂ ከመጀመሪያው እንዲህ አልነበረም።+ ማርቆስ 10:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ፈሪሳውያንም ቀርበው እሱን ለመፈተን በማሰብ አንድ ሰው ሚስቱን እንዲፈታ ሕግ ይፈቅድለት እንደሆነ ጠየቁት።+ ማርቆስ 10:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እነሱም “ሙሴ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ እንዲፈታት ፈቅዷል” አሉት።+