ሉቃስ 6:27, 28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 “ለእናንተ ለምትሰሙ ግን እላችኋለሁ፦ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ፤+ 28 የሚረግሟችሁን መርቁ፤ እንዲሁም ለሚሰድቧችሁ ጸልዩ።+ የሐዋርያት ሥራ 7:60 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 60 ከዚያም ተንበርክኮ በታላቅ ድምፅ “ይሖዋ* ሆይ፣ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው” ብሎ ጮኸ።+ ይህን ከተናገረም በኋላ በሞት አንቀላፋ። ሮም 12:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ስደት የሚያደርሱባችሁን መርቁ፤+ መርቁ እንጂ አትርገሙ።+