31 በዚህ ጊዜ እናቱና ወንድሞቹ+ መጡ፤ ውጭ ቆመውም ሰው ልከው አስጠሩት።+ 32 በዙሪያውም ብዙ ሰዎች ተቀምጠው ስለነበር “እነሆ፣ እናትህና ወንድሞችህ ውጭ ሆነው እየጠሩህ ነው” አሉት።+ 33 እሱ ግን መልሶ “እናቴና ወንድሞቼ እነማን ናቸው?” አላቸው። 34 ከዚያም ዙሪያውን ከበው ወደተቀመጡት ሰዎች ተመልክቶ እንዲህ አለ፦ “እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው!+ 35 የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ ለእኔ ወንድሜ፣ እህቴና እናቴ ነው።”+