ዮሐንስ 20:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “ጥብቅ አድርገሽ አትያዥኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግኩምና። ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ+ ‘ወደ አባቴና+ ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና+ ወደ አምላካችሁ ላርግ ነው’ ብለሽ ንገሪያቸው።” ዕብራውያን 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 የሚቀድሰውም ሆነ የሚቀደሱት ሰዎች፣+ ሁሉም ከአንድ አባት የመጡ ናቸውና፤+ ከዚህም የተነሳ እነሱን ወንድሞች ብሎ ለመጥራት አያፍርም፤+
17 ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “ጥብቅ አድርገሽ አትያዥኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግኩምና። ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ+ ‘ወደ አባቴና+ ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና+ ወደ አምላካችሁ ላርግ ነው’ ብለሽ ንገሪያቸው።”