ማርቆስ 11:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ በጸሎት የምትጠይቁትንና የምትለምኑትን ነገር ሁሉ እንዳገኛችሁት አድርጋችሁ እመኑ፤ ደግሞም ታገኙታላችሁ።+ ሉቃስ 11:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ደጋግማችሁ ለምኑ፣+ ይሰጣችኋል፤ ሳታሰልሱ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ ደጋግማችሁ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።+ ዮሐንስ 14:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 በተጨማሪም አብ በወልድ አማካኝነት እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።+ ያዕቆብ 1:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እንግዲህ ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤+ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ* ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤+ ይህም ሰው ይሰጠዋል።+ 1 ዮሐንስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 እንዲሁም ትእዛዛቱን ስለምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኙትን ነገሮች ስለምናደርግ የምንጠይቀውን ሁሉ ከእሱ እንቀበላለን።+
5 እንግዲህ ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤+ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ* ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤+ ይህም ሰው ይሰጠዋል።+