-
ማርቆስ 14:12-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 የቂጣ በዓል+ በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን፣ እንደተለመደው የፋሲካን መሥዋዕት+ በሚያቀርቡበት ዕለት ደቀ መዛሙርቱ “ፋሲካን እንድትበላ የት ሄደን እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት።+ 13 እሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፦ “ወደ ከተማው ሂዱ፤ በዚያም የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ። እሱንም ተከተሉት፤+ 14 ወደሚገባበት ቤት ሄዳችሁ የቤቱን ጌታ ‘መምህሩ “ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?” ብሏል’ በሉት። 15 እሱም የተነጠፈና የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል። እዚያ አዘጋጁልን።” 16 ደቀ መዛሙርቱም ሄዱ፤ ወደ ከተማውም ገቡ፤ እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።
-
-
ሉቃስ 22:7-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 የቂጣ በዓል የሚከበርበት ቀን ደረሰ፤ በዚህ ዕለት የፋሲካ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር፤+ 8 ስለዚህ ኢየሱስ “ሄዳችሁ ፋሲካን እንድንበላ አዘጋጁልን”+ ብሎ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላካቸው። 9 እነሱም “የት እንድናዘጋጅ ትፈልጋለህ?” አሉት። 10 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ከተማው ስትገቡ የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ። እሱን ተከትላችሁ ወደሚገባበት ቤት ሂዱ።+ 11 የቤቱንም ባለቤት ‘መምህሩ “ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?” ብሎሃል’ በሉት። 12 ሰውየውም የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል፤ በዚያ አዘጋጁ።” 13 እነሱም ሄዱ፤ እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።
-