ማቴዎስ 18:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ስለዚህ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጠው እንደዚህ ትንሽ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ነው፤+ ማቴዎስ 19:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ይሁን እንጂ ኢየሱስ “ልጆቹን ተዉአቸው፤ ወደ እኔ እንዳይመጡ አትከልክሏቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ነውና” አለ።+ ሉቃስ 18:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ይሁን እንጂ ኢየሱስ ሕፃናቱን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አለ፦ “ልጆቹ ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሏቸው፤ የአምላክ መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ነውና።+ 1 ጴጥሮስ 2:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ገና እንደተወለዱ ሕፃናት+ በአምላክ ቃል ውስጥ ለሚገኘው ያልተበረዘ* ወተት ጉጉት አዳብሩ፤ ይህም በእሱ አማካኝነት ወደ መዳን ማደግ እንድትችሉ ነው፤+