የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 61:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 61 የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤+

      ምክንያቱም ይሖዋ የዋህ ለሆኑ ሰዎች ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል።+

      ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣

      ለተማረኩት ነፃነትን እንዳውጅ

      እንዲሁም ‘የእስረኞች ዓይን ይከፈታል’ ብዬ እንድናገር ልኮኛል፤+

  • ማቴዎስ 9:12, 13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ኢየሱስም የተናገሩትን ሰምቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።+ 13 እንግዲያው ሄዳችሁ ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን እንጂ መሥዋዕትን አይደለም’+ የሚለውን ቃል ትርጉም አስተውሉ። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ልጠራ ነውና።”

  • ሉቃስ 5:31, 32
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።+ 32 እኔ የመጣሁት ኃጢአተኞች ንስሐ እንዲገቡ ለመጥራት እንጂ ጻድቃንን ለመጥራት አይደለም።”+

  • ሉቃስ 19:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ምክንያቱም የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ለመፈለግና ለማዳን ነው።”+

  • 1 ጢሞቴዎስ 1:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ‘ክርስቶስ ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ለማዳን+ ወደ ዓለም መጣ’ የሚለው ቃል እምነት የሚጣልበትና ሙሉ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚገባው ነው። ከኃጢአተኞች ደግሞ እኔ ዋነኛ ነኝ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ