ኢሳይያስ 53:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በእርግጥም እሱ ራሱ ሕመማችንን ተሸከመ፤+ሥቃያችንንም ተቀበለ።+ እኛ ግን እንደተቀሰፈ፣ በአምላክ እንደተመታና እንደተጎሳቆለ አድርገን ቆጠርነው። ማቴዎስ 9:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ኢየሱስም የተናገሩትን ሰምቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።+ ማርቆስ 2:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ኢየሱስ ይህን ሲሰማ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ልጠራ ነው” አላቸው።+