13 ሰዎችም ኢየሱስ እጁን እንዲጭንባቸው ትናንሽ ልጆችን ወደ እሱ ያመጡ ጀመር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው።+ 14 ኢየሱስ ይህን ሲያይ ተቆጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ልጆቹ ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሏቸው፤ የአምላክ መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ነውና።+ 15 እውነት እላችኋለሁ፣ የአምላክን መንግሥት እንደ አንድ ትንሽ ልጅ ሆኖ የማይቀበል ሁሉ ፈጽሞ ወደዚህ መንግሥት አይገባም።”+ 16 ልጆቹንም አቀፋቸው፤ እጁንም ጭኖ ባረካቸው።+