ማቴዎስ 24:42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 ስለዚህ ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ ስለማታውቁ ምንጊዜም ነቅታችሁ ጠብቁ።+ ማርቆስ 13:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ስለዚህ የቤቱ ጌታ፣ በምሽት* ይሁን በእኩለ ሌሊት* ወይም ዶሮ ሲጮኽ* ይሁን ከመንጋቱ* በፊት፣ መቼ እንደሚመጣ ስለማታውቁ ምንጊዜም ነቅታችሁ ጠብቁ፤+ ራእይ 6:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ተራሮቹንና ዓለቶቹንም እንዲህ እያሉ ተማጸኑ፦ “በላያችን ውደቁና+ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው+ ፊትና ከበጉ+ ቁጣ ሰውሩን፤ 17 ምክንያቱም ቁጣቸውን የሚገልጹበት ታላቁ ቀን መጥቷል፤+ ማንስ ሊቆም ይችላል?”+ ራእይ 16:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 “እነሆ፣ እንደ ሌባ እመጣለሁ።+ ራቁቱን እንዳይሄድና ሰዎች ኀፍረቱን እንዳያዩበት+ ነቅቶ የሚኖርና+ መደረቢያውን የሚጠብቅ ሰው ደስተኛ ነው።”
16 ተራሮቹንና ዓለቶቹንም እንዲህ እያሉ ተማጸኑ፦ “በላያችን ውደቁና+ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው+ ፊትና ከበጉ+ ቁጣ ሰውሩን፤ 17 ምክንያቱም ቁጣቸውን የሚገልጹበት ታላቁ ቀን መጥቷል፤+ ማንስ ሊቆም ይችላል?”+