23 እኔ ከጌታ የተቀበልኩትን ለእናንተ አስተላልፌአለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት ሌሊት+ ቂጣ አንስቶ 24 ካመሰገነ በኋላ ቆርሶ “ይህ ስለ እናንተ የሚሰጠውን ሥጋዬን ያመለክታል።+ ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።+ 25 በተጨማሪም ራት ከበሉ በኋላ ጽዋውን+ አንስቶ ልክ እንደዚሁ አደረገ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ጽዋ በደሜ+ አማካኝነት የሚመሠረተውን አዲሱን ቃል ኪዳን+ ያመለክታል። ከዚህ ጽዋ በጠጣችሁ ቁጥር ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት።”+