ኢሳይያስ 50:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢም ለሚነጩም ጉንጮቼን ሰጠሁ። ፊቴን፣ ከሚያዋርዱ ነገሮችና ከትፋት አልሰወርኩም።+ ኢሳይያስ 53:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እሱ ግን ስለ መተላለፋችን+ ተወጋ፤+ስለ በደላችን ደቀቀ።+ በእሱ ላይ የደረሰው ቅጣት ለእኛ ሰላም አስገኘልን፤+በእሱም ቁስል የተነሳ እኛ ተፈወስን።+ ማቴዎስ 26:67, 68 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 67 ከዚያም ፊቱ ላይ ተፉበት፤+ በቡጢም መቱት።+ ሌሎቹም በጥፊ እየመቱት+ 68 “ክርስቶስ ሆይ፣ ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደመታህ ንገረን?” አሉት። ማርቆስ 14:65 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 65 አንዳንዶች ይተፉበት ጀመር፤+ ፊቱንም ሸፍነው በቡጢ እየመቱት “ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደመታህ ንገረን!” ይሉት ነበር። የሸንጎው አገልጋዮችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።+
65 አንዳንዶች ይተፉበት ጀመር፤+ ፊቱንም ሸፍነው በቡጢ እየመቱት “ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደመታህ ንገረን!” ይሉት ነበር። የሸንጎው አገልጋዮችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።+