ማቴዎስ 20:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 የሰው ልጅም የመጣው ለማገልገልና+ በብዙ ሰዎች ምትክ ሕይወቱን* ቤዛ አድርጎ ለመስጠት+ እንጂ እንዲገለገል አይደለም።” ዮሐንስ 15:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ሕይወቱን* ለወዳጆቹ ሲል አሳልፎ ከሚሰጥ ሰው የበለጠ ፍቅር ያለው ማንም የለም።+ 1 ዮሐንስ 3:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እሱ ሕይወቱን* ለእኛ አሳልፎ ስለሰጠ በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤+ እኛም ሕይወታችንን* ለወንድሞቻችን አሳልፈን የመስጠት ግዴታ አለብን።+