ዮሐንስ 10:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እኔ ጥሩ እረኛ ነኝ፤+ ጥሩ እረኛ ሕይወቱን* ለበጎቹ ሲል አሳልፎ ይሰጣል።+ ሮም 5:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ለጻድቅ ሰው የሚሞት ማግኘት በጣም አዳጋች ነው፤ ለጥሩ ሰው ለመሞት የሚደፍር ግን ምናልባት ይገኝ ይሆናል። 8 ሆኖም አምላክ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ እንዲሞትልን በማድረግ ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር አሳይቷል።+ ኤፌሶን 5:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ስለዚህ የተወደዳችሁ ልጆቹ በመሆን አምላክን የምትመስሉ ሁኑ፤+ 2 ክርስቶስ እንደወደደንና*+ ጥሩ መዓዛ እንዳለው ሽታ ራሱን ስለ እኛ* መባና መሥዋዕት አድርጎ ለአምላክ እንደሰጠ+ ሁሉ እናንተም በፍቅር መመላለሳችሁን ቀጥሉ።+ 1 ዮሐንስ 3:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እሱ ሕይወቱን* ለእኛ አሳልፎ ስለሰጠ በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤+ እኛም ሕይወታችንን* ለወንድሞቻችን አሳልፈን የመስጠት ግዴታ አለብን።+
7 ለጻድቅ ሰው የሚሞት ማግኘት በጣም አዳጋች ነው፤ ለጥሩ ሰው ለመሞት የሚደፍር ግን ምናልባት ይገኝ ይሆናል። 8 ሆኖም አምላክ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ እንዲሞትልን በማድረግ ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር አሳይቷል።+
5 ስለዚህ የተወደዳችሁ ልጆቹ በመሆን አምላክን የምትመስሉ ሁኑ፤+ 2 ክርስቶስ እንደወደደንና*+ ጥሩ መዓዛ እንዳለው ሽታ ራሱን ስለ እኛ* መባና መሥዋዕት አድርጎ ለአምላክ እንደሰጠ+ ሁሉ እናንተም በፍቅር መመላለሳችሁን ቀጥሉ።+