ኢሳይያስ 26:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ። የእኔ አስከሬኖች ይነሳሉ።+ እናንተ በአፈር ውስጥ የምትኖሩ፣+ተነሱ፤ በደስታም እልል በሉ! ጠልህ እንደ ማለዳ ጠል ነውና፤*ምድርም በሞት የተረቱት ዳግም ሕይወት እንዲያገኙ ታደርጋለች።* ዮሐንስ 5:28, 29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በዚህ አትደነቁ፤ በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣልና፤+ 29 መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ* ደግሞ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።+ የሐዋርያት ሥራ 24:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ደግሞም እነዚህ ሰዎች ራሳቸው ተስፋ እንደሚያደርጉት ጻድቃንም ሆኑ ጻድቃን ያልሆኑ ሰዎች+ ከሞት እንደሚነሱ+ በአምላክ ተስፋ አለኝ። ዕብራውያን 11:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀብለዋል፤+ ሌሎች ወንዶች ግን ቤዛ ተከፍሎላቸው ነፃ መሆን ስላልፈለጉ ከባድ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፤ ይህን ያደረጉት የተሻለ ትንሣኤ ለማግኘት ሲሉ ነው። ራእይ 20:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ከዚያም ሙታንን፣ ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ የመጽሐፍ ጥቅልሎችም ተከፈቱ። ሌላም ጥቅልል ተከፈተ፤ ይህም የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ነው።+ ሙታን በጥቅልሎቹ ውስጥ በተጻፉት ነገሮች መሠረት እንደየሥራቸው ፍርድ ተሰጣቸው።+
19 “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ። የእኔ አስከሬኖች ይነሳሉ።+ እናንተ በአፈር ውስጥ የምትኖሩ፣+ተነሱ፤ በደስታም እልል በሉ! ጠልህ እንደ ማለዳ ጠል ነውና፤*ምድርም በሞት የተረቱት ዳግም ሕይወት እንዲያገኙ ታደርጋለች።*
28 በዚህ አትደነቁ፤ በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣልና፤+ 29 መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ* ደግሞ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።+
35 ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀብለዋል፤+ ሌሎች ወንዶች ግን ቤዛ ተከፍሎላቸው ነፃ መሆን ስላልፈለጉ ከባድ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፤ ይህን ያደረጉት የተሻለ ትንሣኤ ለማግኘት ሲሉ ነው።
12 ከዚያም ሙታንን፣ ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ የመጽሐፍ ጥቅልሎችም ተከፈቱ። ሌላም ጥቅልል ተከፈተ፤ ይህም የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ነው።+ ሙታን በጥቅልሎቹ ውስጥ በተጻፉት ነገሮች መሠረት እንደየሥራቸው ፍርድ ተሰጣቸው።+