ዘሌዋውያን 19:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “‘የሕዝብህን ልጆች አትበቀል፤+ በእነሱም ላይ ቂም አትያዝ፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። ዮሐንስ 15:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ትእዛዜ ይህ ነው፤ እኔ እንደወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።+ 1 ተሰሎንቄ 4:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሁን እንጂ እናንተ ራሳችሁ እርስ በርስ እንድትዋደዱ ከአምላክ ስለተማራችሁ+ የወንድማማች ፍቅርን በተመለከተ+ እንድንጽፍላችሁ አያስፈልግም። ያዕቆብ 2:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እንግዲያው በቅዱስ መጽሐፉ መሠረት “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ የሚለውን ንጉሣዊ ሕግ ተግባራዊ የምታደርጉ ከሆነ መልካም እያደረጋችሁ ነው። 1 ጴጥሮስ 1:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 እንግዲህ ለእውነት በመታዘዝ ራሳችሁን* ስላነጻችሁ ግብዝነት የሌለበት የወንድማማች መዋደድ አላችሁ፤+ በመሆኑም እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ።+ 1 ዮሐንስ 3:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እኛ ወንድሞችን ስለምንወድ+ ከሞት ወደ ሕይወት እንደተሻገርን እናውቃለን።+ ወንድሙን የማይወድ በሞት ውስጥ ይኖራል።+