ማቴዎስ 7:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “ደጋግማችሁ ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤+ ሳታቋርጡ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ ደጋግማችሁ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።+ ዮሐንስ 16:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 በዚያን ጊዜ እኔን ምንም ጥያቄ አትጠይቁኝም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አብን ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትጠይቁት+ ይሰጣችኋል።+