ዮሐንስ 8:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 በዚህ ጊዜ “አባትህ የት ነው?” አሉት። ኢየሱስም “እናንተ እኔንም ሆነ አባቴን አታውቁም።+ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር”+ ሲል መለሰላቸው። ዮሐንስ 15:20, 21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ባሪያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን ቃል አስታውሱ። እኔን ስደት አድርሰውብኝ ከሆነ እናንተንም ስደት ያደርሱባችኋል፤+ ቃሌን ጠብቀው ከሆነ ደግሞ የእናንተንም ቃል ይጠብቃሉ። 21 ሆኖም የላከኝን ስለማያውቁት በስሜ ምክንያት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያደርጉባችኋል።+ ሮም 10:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ለአምላክ ቅንዓት እንዳላቸው እመሠክርላቸዋለሁና፤+ ሆኖም ቅንዓታቸው በትክክለኛ እውቀት ላይ የተመሠረተ አይደለም። 1 ቆሮንቶስ 2:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይህን ጥበብ ከዚህ ሥርዓት* ገዢዎች መካከል አንዳቸውም አላወቁትም፤+ ቢያውቁትማ ኖሮ ታላቅ ክብር ያለውን ጌታ ባልሰቀሉት* ነበር።
19 በዚህ ጊዜ “አባትህ የት ነው?” አሉት። ኢየሱስም “እናንተ እኔንም ሆነ አባቴን አታውቁም።+ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር”+ ሲል መለሰላቸው።
20 ባሪያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን ቃል አስታውሱ። እኔን ስደት አድርሰውብኝ ከሆነ እናንተንም ስደት ያደርሱባችኋል፤+ ቃሌን ጠብቀው ከሆነ ደግሞ የእናንተንም ቃል ይጠብቃሉ። 21 ሆኖም የላከኝን ስለማያውቁት በስሜ ምክንያት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያደርጉባችኋል።+