ዮናስ 1:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ይሖዋም ዮናስን እንዲውጠው አንድ ትልቅ ዓሣ ላከ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ቆየ።+ ዮናስ 2:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በኋላም ይሖዋ ዓሣውን አዘዘው፤ ዓሣውም ዮናስን በደረቅ ምድር ላይ ተፋው። የሐዋርያት ሥራ 2:23, 24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ይህ ሰው ለሞት አልፎ ተሰጠ። ይህም አምላክ አስቀድሞ የወሰነው ፈቃዱና* የሚያውቀው ነገር ነበር።+ እናንተም በክፉ ሰዎች እጅ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።+ 24 አምላክ ግን ከሞት ጣር* አላቆ አስነሳው፤+ ምክንያቱም ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለም።+
23 ይህ ሰው ለሞት አልፎ ተሰጠ። ይህም አምላክ አስቀድሞ የወሰነው ፈቃዱና* የሚያውቀው ነገር ነበር።+ እናንተም በክፉ ሰዎች እጅ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።+ 24 አምላክ ግን ከሞት ጣር* አላቆ አስነሳው፤+ ምክንያቱም ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለም።+