ማቴዎስ 28:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ይሁንና የኢየሱስ 11 ደቀ መዛሙርት ከእሱ ጋር ለመገናኘት በገሊላ ወደሚገኘው፣ እሱ ወደነገራቸው ተራራ ሄዱ።+ የሐዋርያት ሥራ 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 መከራ ከተቀበለ በኋላ ሕያው መሆኑን በብዙ አሳማኝ ማስረጃዎች አሳያቸው።+ እነሱም ለ40 ቀናት ያዩት ሲሆን እሱም ስለ አምላክ መንግሥት ይነግራቸው ነበር።+ የሐዋርያት ሥራ 3:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በአንጻሩ ግን የሕይወትን “ዋና ወኪል”*+ ገደላችሁት። አምላክ ግን ከሞት አስነሳው፤ እኛም ለዚህ ነገር ምሥክሮች ነን።+ 1 ቆሮንቶስ 15:4-7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ደግሞም ተቀበረ፤+ ቅዱሳን መጻሕፍት+ እንደሚሉትም በሦስተኛው ቀን+ ተነሳ፤+ 5 ለኬፋ*+ ከዚያም ለአሥራ ሁለቱ ታየ።+ 6 በኋላ ደግሞ በአንድ ጊዜ ከ500 ለሚበልጡ ወንድሞች የታየ+ ሲሆን አንዳንዶቹ በሞት ቢያንቀላፉም አብዛኞቹ ግን አሁንም ከእኛ ጋር አሉ። 7 ከዚያም ለያዕቆብ ታየ፤+ ቀጥሎም ለሐዋርያቱ በሙሉ ታየ።+
4 ደግሞም ተቀበረ፤+ ቅዱሳን መጻሕፍት+ እንደሚሉትም በሦስተኛው ቀን+ ተነሳ፤+ 5 ለኬፋ*+ ከዚያም ለአሥራ ሁለቱ ታየ።+ 6 በኋላ ደግሞ በአንድ ጊዜ ከ500 ለሚበልጡ ወንድሞች የታየ+ ሲሆን አንዳንዶቹ በሞት ቢያንቀላፉም አብዛኞቹ ግን አሁንም ከእኛ ጋር አሉ። 7 ከዚያም ለያዕቆብ ታየ፤+ ቀጥሎም ለሐዋርያቱ በሙሉ ታየ።+