28 ከዚያ በኋላ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁ፤+
ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤
ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፤
ወጣቶቻችሁም ራእዮችን ያያሉ።+
29 በዚያ ቀን በወንዶች ባሪያዎቼና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ሳይቀር
መንፈሴን አፈሳለሁ።
30 በሰማያትና በምድር ድንቅ ነገሮች አሳያለሁ፤
ደም፣ እሳትና የጭስ ዓምድ ይታያል።+
31 ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን+ ከመምጣቱ በፊት
ፀሐይ ወደ ጨለማ፣ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።+
32 የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤+
ይሖዋ እንደተናገረው በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚድኑ+ ይኸውም
ይሖዋ የሚጠራቸው ከጥፋት የሚተርፉ ሰዎች ይኖራሉ።”