ዘዳግም 18:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 አምላክህ ይሖዋ ከወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል። እናንተም እሱን ማዳመጥ ይኖርባችኋል።+ መዝሙር 16:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 መቃብር* ውስጥ አትተወኝምና።*+ ታማኝ አገልጋይህ ጉድጓድ እንዲያይ* አትፈቅድም።+ ኢሳይያስ 7:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በመሆኑም ይሖዋ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፦ እነሆ፣ ወጣቷ* ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤+ አማኑኤል* ብላም ትጠራዋለች።+ ሚክያስ 5:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ከይሁዳ አእላፋት* መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽውቤተልሔም ኤፍራታ+ ሆይ፣ምንጩ ከጥንት፣ ከረጅም ዘመን በፊት የሆነ፣በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል።+
2 ከይሁዳ አእላፋት* መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽውቤተልሔም ኤፍራታ+ ሆይ፣ምንጩ ከጥንት፣ ከረጅም ዘመን በፊት የሆነ፣በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል።+