2 የበላይ ተመልካቾች ሆናችሁ በማገልገል በአደራ የተሰጣችሁን የአምላክን መንጋ እንደ እረኞች ሆናችሁ ተንከባከቡ፤+ ሥራችሁን በግዴታ ሳይሆን በአምላክ ፊት በፈቃደኝነት ተወጡ፤+ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በመመኘት ሳይሆን+ ለማገልገል በመጓጓት፣ 3 የአምላክ ንብረት በሆኑት ላይ ሥልጣናችሁን በማሳየት ሳይሆን+ ለመንጋው ምሳሌ በመሆን ጠብቁ።+ 4 የእረኞች አለቃ+ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋ የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።+