የሐዋርያት ሥራ 9:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ+ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመቀላቀል ጥረት አደረገ፤ እነሱ ግን ደቀ መዝሙር መሆኑን ስላላመኑ ሁሉም ፈሩት። ገላትያ 1:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከዚያም ከሦስት ዓመት በኋላ ኬፋን*+ ለመጠየቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ፤+ ከእሱም ጋር 15 ቀን ተቀመጥኩ።