-
ኤፌሶን 1:9-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ይህን ያደረገው የፈቃዱን ቅዱስ ሚስጥር ለእኛ በማሳወቅ ነው።+ ይህ ሚስጥር ደግሞ እሱ ራሱ ካሰበው ዓላማው ጋር የሚስማማ ነው፤ 10 ዓላማውም በተወሰኑት ዘመናት ማብቂያ ላይ አንድ አስተዳደር ለማቋቋም ይኸውም ሁሉንም ነገሮች ማለትም በሰማያት የሚሆኑ ነገሮችንና በምድር የሚሆኑ ነገሮችን በክርስቶስ አንድ ላይ ለመሰብሰብ ነው።+ አዎ፣ በእሱ አማካኝነት ሁሉም ነገሮች ይሰበሰባሉ፤ 11 እኛም ከእሱ ጋር አንድነት ያለን ሲሆን ወራሾች እንድንሆንም ተመርጠናል፤+ ምክንያቱም ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ሁሉንም ነገር በወሰነው መንገድ የሚያከናውነው እሱ ከዓላማው ጋር በሚስማማ ሁኔታ አስቀድሞ መርጦናል፤ 12 ይህም የሆነው በክርስቶስ ተስፋ በማድረግ የመጀመሪያ የሆንነው እኛ አምላክን ከፍ ከፍ እንድናደርግና እንድናወድስ ነው።
-