ዘኁልቁ 21:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ሕዝቡም እንዲህ በማለት በአምላክና በሙሴ ላይ ያማርር ጀመር፦+ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብፅ ያወጣችሁን ለምንድን ነው? ምግብ የለ፣ ውኃ የለ፤+ ደግሞም ይህን የማይረባ ምግብ ጠልተነዋል።”*+ 6 በመሆኑም ይሖዋ በሕዝቡ ላይ መርዘኛ* እባቦችን ሰደደባቸው፤ እባቦቹም ሰዎቹን ስለነደፏቸው ብዙ እስራኤላውያን ሞቱ።+ ዘዳግም 6:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “በማሳህ እንደተፈታተናችሁት+ አምላካችሁን ይሖዋን አትፈታተኑት።+ ማቴዎስ 4:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ኢየሱስም “‘አምላክህን ይሖዋን* አትፈታተነው’ ተብሎም ተጽፏል” አለው።+
5 ሕዝቡም እንዲህ በማለት በአምላክና በሙሴ ላይ ያማርር ጀመር፦+ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብፅ ያወጣችሁን ለምንድን ነው? ምግብ የለ፣ ውኃ የለ፤+ ደግሞም ይህን የማይረባ ምግብ ጠልተነዋል።”*+ 6 በመሆኑም ይሖዋ በሕዝቡ ላይ መርዘኛ* እባቦችን ሰደደባቸው፤ እባቦቹም ሰዎቹን ስለነደፏቸው ብዙ እስራኤላውያን ሞቱ።+