ማቴዎስ 5:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ክፉን ሰው አትቃወሙት፤ ከዚህ ይልቅ ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሌላኛውን ደግሞ አዙርለት።+ ያዕቆብ 1:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን እወቁ፦ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየና+ ለቁጣ የዘገየ መሆን አለበት፤+