የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 12:1-3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ይሖዋም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ከአገርህ፣ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤት ወጥተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።+ 2 አንተን ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ፤ አንተም በረከት ትሆናለህ።+ 3 የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግምህንም እረግማለሁ፤+ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በአንተ አማካኝነት ይባረካሉ።”*+

  • ዘፍጥረት 12:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ይሖዋም ለአብራም ተገለጠለትና “ይህችን ምድር ለዘርህ+ እሰጣለሁ”+ አለው። ስለዚህ አብራም ተገልጦለት ለነበረው ለይሖዋ በዚያ መሠዊያ ሠራ።

  • ዘፍጥረት 13:14, 15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ሎጥ ከአብራም ከተለየ በኋላ ይሖዋ አብራምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ ካለህበት ቦታ ሆነህ ዓይንህን አቅንተህ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ተመልከት፤ 15 ምክንያቱም የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘለቄታው ርስት አድርጌ እሰጣለሁ።+

  • ዘፍጥረት 17:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 “ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህ አምላክ እሆን ዘንድ በእኔና በአንተ እንዲሁም መጪዎቹን ትውልዶቻቸውን ሁሉ ጨምሮ ከአንተ በኋላ በሚመጡት ዘሮችህ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አድርጌ እጠብቀዋለሁ።+

  • ዘፍጥረት 22:17, 18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ በእርግጥ አበዛዋለሁ፤+ ዘርህም የጠላቶቹን በር* ይወርሳል።+ 18 ቃሌን ስለሰማህ የምድር ብሔራት ሁሉ በዘርህ+ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።’”+

  • ዘፍጥረት 24:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ከአባቴ ቤትና ከዘመዶቼ አገር ያወጣኝ+ እንዲሁም ‘ይህን ምድር+ ለዘርህ+ እሰጣለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ+ የሰማይ አምላክ ይሖዋ መልአኩን ከፊትህ ይልካል፤+ አንተም ከዚያ አገር+ ለልጄ ሚስት ታመጣለታለህ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ