ምሳሌ 6:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፤የእናትህንም መመሪያ* ቸል አትበል።+ ሉቃስ 2:51 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 51 ከዚያም ኢየሱስ አብሯቸው ወደ ናዝሬት ተመለሰ፤ እንደ ወትሮውም ይገዛላቸው* ነበር።+ እናቱም የተባሉትን ነገሮች ሁሉ በልቧ ትይዝ ነበር።+ ኤፌሶን 6:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ልጆች ሆይ፣ ከጌታ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤+ ይህ የጽድቅ ተግባር ነውና።